አንድ ጊዜ አሜሪካን ሀገር በነበረ ስብሰባ ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት
የተመዘገበው በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ትክክል እንዳልሆነ ትንሽ ጠንከር ያለ ሃሳብ ሰጠው፡፡ በቂ ምክንያት ነበረኝ፣ አሁንም ልክ
እንደሆንኩ ይስማኛል፡፡ ኮንዶሚኒየም የሚሰረው በመንግሰት ልዩ ድጋፍ “ለድሆች” በሚል ነበር፡፡ ነበር ያልኩት እየገቡ ያሉት እንማን
እንደሆኑ በብዛት ስለሚታወቅ ነው፡፡ ስለዚ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ በአንፃራዊነት የተሻሉ ናቸው፡፡ ሰለዚህ በዚህ ውድድር
ውስጥ መግባት የለባቸውም የሚለው አንዱ ለሰጠሁት ሃሳብ መነሻ ሲሆን፡፡ ዋነኛውም ግን መንግሰት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን/ትውልደ
ኢትዮጵያዊያን ለማገዝ ፈልጎ ሳይሆን በዚሁ መስመር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ነው፡፡ የሚሉ ሃሳቦች ነበሩኝ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ከእውነቱ
እና ከቀረበው አምክንዮ ይልቅ የግል ጥቅሙ በልጦበት እጅጉን ቅር ተሰኘ፡፡ ድሮም እኔ በውሸት ለማስደስት ሰለአልተዘጋጀሁ በግሌ
ደስ አለኝ፡፡ ተዋወቅን ብል ነው ደስ የሚለኝ፡፡ ይህን አስመልክቶ በግል እንዲህ ዓይነት አቋም አትያዝ ውጭ ያሉት ሰዎች ቅር ይላቸዋል፣
ድጋፍም አይሰጡህም የሚሉ ምክር አዘል መልዕክቶች ደርሰውኛል፡፡ እውነቱ ግን ይህው ነበር፡፡ በግሌ የተለየ ድጋፍ ሰለማልፈልግ እውነቱን
መናገር ምርጫያ ነበር፡፡
ሰሞኑን ደግሞ በሀገር ውስጥ ያሉ በመንግሰት ፍርጃ “ጥቅመኞች፣የኒዎ
ሊብራል አቀንቃኞች፣ ወዘተ” የሚባሉት የእኔ ቢጤዎች ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት በ40/60 ቤት ተሰርቶ እንደሚሰጣቸው እንዲሁም
በማህበር ተደራጅተው ሃምሳ ከመቶ (50/50) የግንባታ ወጪ በዝግ ሂስባ ካስቀመጡ በከተማው መሃል ለልማት ከሚነሱት ቦታዎች ቦታ
ይሰጣችኋል ተብለው እጅግ ብዙ ገንዘብ እንዲቆጥቡ አማላይ ሃሳብ ቀረቦላቸው ተግባራዊ ሲያደርጉ ነበር፡፡
አብዛኛው ያለምንም ማንገራገር የመንግሰትን መግለጫ ሰምቶ ቁጠባ ጀመረ-
ቁጠባ ከሚባል ያለውን ጥሪት ተበድሮ ጭምር ወደ ንግድ ባንክ አዞረ ማለት ይቀላል፡፡ በእሩጫ ውድድር አሯሯጭ እንደሚመደበው አንድ
አሯሯጭ ዜናም አብሮ ቀረበ፤ “ቀድሞ ሙሉ የከፈለ ቅድሚያ ያገኛል” የሚል ወሬ ሚዲያውን ጨምሮ በልዩ ልዩ መስመር ተወራ፡፡ በእውነትም
በአስር ሺዎች ሙሉ በሙሉ ከፈሉ፡፡ ለመክፈል ያልቻሉም የቻሉትን ያህል ለመክፈል ተረባረቡ፤ በተለይ አርባ ከመቶ ለማሟላት የሚችሉትን
ሁሉ አደረጉ፡፡ አብዮታዊው ዲሞክራሲው መንግሰታችን “የእነዚህን ጥቅመኞች እና የኒዎ ሊብራሎችን” ገንዘብ ሰብሰቦ በእጁ አስገባ፡፡
በእጅ አዙር በቁጥጥር ስር አዋላቸው ነው መባል ያለበት፡፡
መንግሰት ገንዘቡን ለመሰለውና ለፖለቲካ ጥቅሜ ያዋጣኛል ባለው መስመር
ተጠቀመበት፡፡ ይህን እውነት ከማመን ይልቅ ሁለት ሺ ለማይሞላ ቤት አሰር ሺዎች ይራኮታሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ መንግሰት በሚቀጥሉትም
አምስት አመታት ቤት ሰርቶ እንደማያስረክብ የታመነ ነው፡፡ ለምሳሌ ባለፉ አስር ዓመታት መንግሰት መገንባት የቻለው 175 ሺ የማይበልጥ
ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት የታቀደው ደግሞ 450 ሺ ቤት ለመገንባት ነው፡፡ እንደምታውቁት ፉከራ ነው፡፡ በመጨረሻው ልምድ አግኝተንበታል
ነው የምንባል፡፡ ሚሊዮኖች ተመዝግበው እየጠበቁ ሌሎች ሚሊዮኖች ደግሞ የቤት ፈላጊ ሆነው በዚህ መስመር ቤት አገኛለሁ ማለት የእልም
እንጀራ ይመስለኛል፡፡ ጥቂቶች ቤት አያገኙም እያልኩ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ውጤቱን ግን ወደፊት እናየዋለን፡፡
በነገራችን ላይ መንግሰት ይህን ማድረግ የማይችል መሆኑን በደንብ ተረድተው
በሪል ሰቴት ልማት ውስጥ የሚሰማሩ ኢንቨሰተሮችን በሆነው ባልሆነ እንዳይሳካላቸው መንገድ የሚዘገው መንግሰት መሆኑን ብዙዎች አይረዱም፡፡
ይልቁንም ከቤት አልሚዎች ጋር ከመንግሰት ጋር ተባብረው ፈጣሪ ኢንቨሰተሮችን ያዋክባሉ፡፡ ይሰቀል፣ በድንጋይ ይወገሩ የሚሉ ሞልተዋል፡፡
መንግሰት በዚህ ጊዜ ደግሞ ቤት እንዲያገኙ ፍላጎት እንዳለው መስሎ ቀርቦ ድብቅ ተልዕኮውን ያሳካል፡፡ መንግሰት ይህን የሚያደርገው
የግል አልሚዎች በተሻለ መፈፀም ከቻሉ መሰታውት ሆነው እንደሚያጋልጡት ስለሚረዳ ነው፡፡ ቀደም ሲል የመሬት ዋጋ በማሰወደድ የግል
አልሚዎችን ማሰወጣት በቂ ነው በሚል እየሰራ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ግን በቂ አለመሆኑን በመረዳት በአሁኑ ጊዜ የግል አልሚዎች በፍፁም
እንዳይሳካላቸው እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህን ለመመልከት ግን በፍፁም ከግል ጥቅማችን እና ጉዳታችን ወጥተን ጉዳዩን በእውነት ለመመልከት
ስንወሰን የሚገባን ሚስጥር ነው፡፡
መንግሰት ለቤት አልሚዎች መሬት በነፃ ሰጥቶ አልሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ
ቤት እንዲያቀርቡ ለምን አይደራደርም? ይህማ የኒዎ ሊብራል አስተሳሰብ ነው፡፡ መንግሰት የእኔ ነው በሚለው መሬት ግለሰቦች ሊከብሩበት
የሚል የምቀኛ አስተሳሰብ በውሰጣችን አለ፡፡ መንግሰት ይህን እየኮተኮተ ያሳድጋል፡፡ እኛ ከስር ከስር ውሃ እናጠጣለን፡፡ ተቃቅፈን
በድህነት የመንግሰት ጥገኛ ሆነን እንኖራለን፡፡ መንግሰትም የሚፈልገው ሁላችንንም ግቡ-ውጡ በሚለን መስመር እንድንገኝ ነው፡፡ የምርጫ
ሰሞን ኮንዶሚኒየም ጊቢዎች ውስጥ ያለውን ውክቢያና ጥርነፈ የተመለከተ ነፃነቱን በገንዘቡ አሳልፎ እንደሰጠ ይረዳል፡፡ ኮንዶሚኒየም
ቤት ደርሶት ያከራየ ሁሉ ተከራይም ኢህአዴግን መምረጥ እንዳለበት ማሳሰቢያ የሚሰጡበት ወቅት ነው፡፡
በነገራችን ላይ በዚህ አጋጣሚ የአያት የመኖሪያ መንደር መስራች በግሌ
በግፍ እንደተሰቃዩ ይሰማኛል፡፡ ባደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በሀገራችን የቤት ልማት ውስጥ ማንም በሸፍፅ የማይሽርው አሻራ አኑረዋል፡፡
እጅግ ብዙዎችን ባለቤት/ባለሀገር አድርገዋል፡፡ ይህን የሚያክል የከተማ ክፍል ሲገነቡ ምንም ስህተት አልሰሩም ብዬ መከራከር የምችልበት
መረጃ ባይኖረኝም፣ መንግሰት ይህን የሚያክል ከተማ ክፍል የመገንባት ሰራ ቢሰራ ሊያጠፋ የሚቸለውን ሳሰበው ይዘገንነኛል፡፡ ሰራ
እና ሃሳብ ፈጣሪዎቻችንን ከመሸለም እና እውቅና ከመስጠት ይልቅ ወህኒ ማውረድ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ክብር ለሚገባው ክብር
እንስጥ!!!!
ቸር ይግጠመን!!!!
No comments:
Post a Comment